Fana: At a Speed of Life!

የክልል መንግስታት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ኃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልል መንግስታት አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ኃዘን ገለጹ።
የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በማረፋቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
በተመሳሳይም የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በአቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሀዘን በክልሉ ህዝብና መንግስት ስም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር÷ በቅዱስነታቸው ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው÷ ለመላዉ የእምነቱ ተከታዮች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

 

በተመሳሳይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ከስደት በፊት፣ በስደት ጊዜ እና ከስደት በኋላ በኢትዮጵያ በነበራቸው አገልግሎት፣ ስለሀገርም በነበራቸው ጸሎትና ቡራኬ ትውልድ ሁሉ በታሪክ መዝገብ ሲያስታውሳቸው የሚኖር ታላቅ ቅዱስ አባት እንደሆኑ የክልሉ መንግሥትና ህዝብ ይገነዘባል ብሏል፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት በድጋሜ የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንዲሁም ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን መጽናናትን ተመኝቷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.