Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እስካሁን 20 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ወስደዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እስካሁን 20 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት መውሰዳቸውን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
 
በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ የ2ኛውን ዙር የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ዘመቻን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ በአገሪቱ እስካሁን 25 ሚሊየን 433 ሺህ 752 ዶዝ ክትባት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
 
በዚህ መሰረት ክትባቱ ለ20 ሚሊየን 837 ሺህ 740 ዜጎች መሰጠቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ÷ 192 ሺህ ለሚሆኑት ደግሞ የማጠናከሪያ ክትባት ተሰጥቷል ብለዋል።
 
በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሲባል ክትባቱን በስፋት በማስገባት ለዜጎች እንዲዳረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
 
የክትባት አሰጣጡን ለማስፋትም በዘመቻ እየተሰጠ ሲሆን÷ ሁለተኛውን ዙር የክትባት ዘመቻም ላለፉት ሳምንታት ሲሰጥ መቆየቱ ተመላክቷል፡፡
 
በዚህ ዘመቻ ከ14 ሚሊየን በላይ ዜጎች ክትባት የተሰጠ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥም 12 ሚሊየኑ አዲስ የተከተቡ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
 
ይህም ከሁለት ሳምንት በፊት የተጀመረው ሁለተኛው ዙር የክትባት ዘመቻ ውጤታማ እንደሆነ የሚይሳይ ነው ተብሏል።
 
ለውጤቱ በመጀመሪያ ዙር የታዩ ችግሮችን በመለየትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ውጤት ማምጣት ተችሏልም ብለዋል ዳይሬክተሩ።
 
ለዘመቻው 20 ሚሊየን ክትባት ወደ ክልሎች የተሰራጨ ሲሆን አፋር፣ ሲዳማ እና ደቡብ ክልሎች የተሻለ አፈጻጸም ማሳየታቸው ተገልጿል።
 
የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቆጣጠር ክትባቱን መውሰድ አስፈላጊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ክትባቱ በሚሰጥባቸው ማዕከላት በመገኘት እንዲወስድም ጥሪ ቀርቧል፡፡
 
 
 
በሃይማኖት ኢያሱ
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.