Fana: At a Speed of Life!

በሰባት ወራት ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ከዳያስፖራው ተልኳል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
በበጀት ዓመቱም አራት ቢሊየን ዶላር ከሬሚታንስ ለመሰብሰብ መታቀዱን አመላክቷል።
በተያያዘም በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት 4 ሺህ 83 የዳያስፖራ አባላት በአገር ውስጥ በሚገኙ ባንኮች 4 ሚሊየን 953 ሺህ 333 ዶላር ተቀማጭ እንዲያደርጉ ታቅዶ 4 ሺህ 7 ዳያስፖራዎች ከ3 ሚሊየን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸውን ገልጿል።
ዳያስፖራው በ’አይዞን ኢትዮጵያ’ የበይነ መረብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ አማራጭ እና በውጭ አገራት በሚገኙ ሚሲዮኖች አማካኝነት ለተፈናቀሉ ዜጎችና ለተጎዱ መሰረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ የሚውል ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በገንዘብና በአይነት ድጋፍ ማድረጉን ኤጀንሲው አስታውቋል።
በ’አይዞን ኢትዮጵያ’ የበይነ መረብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ አማራጭ ከ6 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ከ25 ሺህ 400 በላይ ዳያስፖራዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች መሰብሰቡ ተጠቁሟል።
ዳያስፖራው በሰባት ወሩ ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሕልውና ዘመቻ ከ109 ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብና አይነት ድጋፍ ማድረጉን ነው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ያስታወቀው።
በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት በኢንቨስትመንትና ንግድ ላይ ለመሰማራት 895 ዳያስፖራዎች ፍላጎት ማሳየታቸውንም አመላክቷል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ለኢትዮጵያ ልማትና እድገት እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.