Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ ሀይል ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ ነው – የገንዘብ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ትኩረት በተሰጠው የኢነርጂ ዘርፍ ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ ሀይል ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ገለፁ፡፡
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የ2014 በጀት አመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ዛሬ በሂልተን ሆቴል በገንዘብ ሚኒስቴርና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ተገምግሟል፡፡
 
በዚህ ወቅት ሚኒሰትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እንደገለጹት፥ መንግስት ለሀይል ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠ በመሆኑ በጥንቃቄ የሚከታተለውና የሚመራው ዘርፍ ነው፡፡
 
በሀይል ማመንጨትና ማሰረጫት ዘርፍ ያለው የሪፎርም ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና የዘርፉ የፕሮጀክት አመራርና አፈጻጸም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባው ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡
 
በሁለቱም ተቋማት በኩል ከደንበኞች ያልተሰበሰበው ገንዘብ በጊዜ እንዲሰበሰብ በተለይም ወደ ጎረቤት ሀገሮች ከተላከው ሀይል ያልተሰበሰበውን ገንዘብ ተከታትሎ ገቢ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
 
የሀይል ብክነትንና መቆራረጥን መቆጣጠር፣ ወጪ ቅነሳን ተግባራዊ ማድረግ፣ በክልሎች ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የዘርፉን ያልተማከለ አስተዳደር አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አቶ አህመድ ጠቁመው፥ ገንዘብ ሚኒስቴርም ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ ለተቋማቱ እንደሚሰጥ ማረጋገጣቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.