Fana: At a Speed of Life!

የበልግ አብቃይ አካባቢዎች በሚቀጥሉት 10 ቀናት ዝናብ ያገኛሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገሪቷ የበልግ አብቃይ አካባቢዎች በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ ዝናብ እንደሚያገኙ ብሔራዊ የሚቲዮሮሎጂ ኢኒስቲቲዩት አስታወቀ፡፡

ኢኒስቲቲዩት እንዳስታወቀው በተጠቀሱት ቀናት ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉአባቦር፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምሥራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሁሉም ዞኖች እንዲሁም አዲስ አበባ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

ከዝናብ ሥርጭቱ በአገሪቷ የበልግ አብቃይ አካባቢዎች በተለይ የሰሜን ምሥራቅ፣ የምሥራቅ፣ ደቡብና የደቡብ ምሥራቅ የአገሪቱ ክፍሎች በመጠንም ይሁን በሥርጭት የተጠናከረ እርጥበት ማግኘት የሚጀምሩበት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በተመሳሳይ በመጋቢት ወር በርካታ የአገሪቷ አካባቢዎች ዝናብ እንደሚያገኙም ኢኒስቲቲዩቱ ጠቅሷል፡፡

በዚሁም ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሊአባቦር፣ ምዕራብና ምሥራቅ ወለጋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የአርሲና የባሌ፣ የቦረናና የጉጂ ዞኖች፣ ከአፋር ዞን 3 እና 5፣ ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር እንዲሁም የባህርዳር ዙሪያ ከመደበኛ ጋር የተቀራረበና በጥቂት ሥፍራዎች ደግሞ ከመደበኛው በታች ዝናብ የሚያገኙ መሆኑንም ኢኒስቲቲዩቱ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በአዲስ አበባ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሁሉም ዞኖችና የጋምቤላ ክልል በአብዛኛው አካባቢዎች ከመደበኛ ጋር የተቀራረበና በጥቂት ሥፍራዎች ደግሞ ከመደበኛው በታች ዝናብ እንደሚያገኙም ነው ያስታወቀው፡፡

ቀሪዎቹ የአገሪቷ አካባቢዎች በአመዛኙ ደረቅ ሆነው እንደሚሰነብቱ ትንበያው ያሳየ ሲሆን÷ከዝናብ ሥርጭቱ የሚገኘውን ውሃ በአግባቡ በመያዝ ጥቅም ላይ እንዲውል ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.