Fana: At a Speed of Life!

የዘይት ፋብሪካዎች የሀገር ውስጥ የዘይት ፍጆታን ይሸፍናሉ የሚል ተስፋ ቢጣልባቸውም ይህንን ማሳካት አልቻሉም

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተቋቋሙ የዘይት ፋብሪካዎች የሀገር ውስጥ የዘይት ፍጆታን ይሸፍናሉ የሚል ተስፋ ቢጣልባቸውም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ይህንን ማሳካት አልቻሉም፡፡

በዚህም የሀገሪቱን 60 ከመቶ የዘይት አቅርቦት የመሸፈን አቅም እንዳለዉ የተነገረለት የፌቤላ የዘይት ፋብሪካ በውሱን በማምረት ላይ ቢሆንም የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ተግዳሮት እንደሆነበት ያነሳል፡፡

የፌቤላ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንየዉ ዋሴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ በተለይም የመብራት መቆራረጥ ፈተና መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ እስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻም ችግሩ እንደሚታወቅ ነው የገለፁት፡፡

በተፈጠሩ ሀገራዊ ሁኔታዎች ሳቢያም ስራዎች መዘግየታቸውን ጠቅሰው ከችግሩ አሳሳቢነትና አንገብጋቢነት አኳያ በከፍተኛ ትኩረት እየሰራን ነው ብለዋል።

በመሀመድ አሊ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.