Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777-8 የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላን ለመግዛት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777-8 አዲስ የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላን ለመግዛት የሚያስችለውን ስምምነት ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር ተፈራረመ።
ስምምነቱ አየር መንገዱን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከመጣው የካርጎ ጭነት አገልግሎት ፍላጎት ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ሲሆን፥ እያስመዘገበ የሚገኘውንም ዕድገትም ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ “በአፍሪካ አቪየሽን መስክ ቀዳሚ አየር መንገድ እንደመሆናችን መጠን ይህንን አዲስ፣ ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ የጭነት አውሮፕላን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረማችን ደስታ ይሰማናል” ብለዋል፡፡
“ይህ አዲሱ ቦይንግቨ777-8F የጭነት አውሮፕላን እያደገ የመጣውን የአየር መንገዱን የካርጎ ጭነት አገልግሎት በማስፋፋት አሁን ያሉትን 66 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ለማሳደግ በእጅጉ ይረዳዋል” ማለታቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.