Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የብዝሃነት ፎረም በድሬዳዋ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ድሬዳዋን ጨምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የብዝሃነት ፎረም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ ፡፡
ፎረሙ አካታችነትን በማረጋገጥ ብዝሃነትን በማጎልበት የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ያስችላል በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው፡፡
በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ÷ ብዝሃት ቀን ተለይቶለት የሚከበር ሳይሆን የዕለት ተዕለት ሥራችን አድርገን ልንተገብረው ይገባል ብለዋል፡፡
በተለይም እንደ ህንድና ከመሳሰሉት ብዝሃነትን በሚገባ እየተገበሩ ከሚገኙ ሀገራት ኢትዮጵያ ልምድ ልትቀምር እንደሚገባም አመላተዋል፡፡
ልማቷ የተረጋገጠች ሃገርን ለመፍጠር ብዝሃት ላይ አተኩሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ የገለጹት ደግሞ÷ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡኽ÷ ብዝሃነትን ወደ ዕድል በመቀየር መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደም በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ ያላትን ብዝሃት ለዕድገቷ ትጠቀም ዘንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የጎላ ነው ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ይህን ድርሻ ለመወጣት በማሰብም የብዝሃነት ፎረሙን ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.