Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን በማባዛት የተጠረጠሩ 2 የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ከተማ ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያባዙ ነበር የተባሉ 2 የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፡፡

የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ እንዳሉት ÷ግለሰቦቹ የናይጀሪያ እና የኮንጎ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ ÷ኅብረተሰቡ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት የፌደራልና የክልሉ ፖሊስ በግለሰቦቹ ላይ ክትትል በማድረግ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በወቅቱም ባለ 100 የአሜሪካ ዶላር፣ 5 ሺህ የኡጋንዳ ገንዘብ፣ አንድ የደቡብ ሱዳን ፓውንድ፣ 200 የኢትዮጵያ ብር በተለያዩ ብልቃጦች የተዘጋጀ ፈሳሽና ዱቄት ኬሚካል መሳይ፣ ማስመሪያ እና በርካታ ካኪ ፖስታዎችን በማስረጃነት መያዛቸውን ገልፀዋል፡፡

የኮንጎ ዜግነት ያለው ግለሠብ የስደተኛ መታወቂያ የያዘ መሆኑን አቶ ኡገቱ አስታውቀው ግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን አመልክተዋል።

ኅብረተሰቡ መሰል የማጭበርበር የወንጀል ሰለባ እንዳይሆን ጥንቃቄ እንዲያደርግና ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም ጥቆማ እንዲሰጥም ጥሪ ቀርቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.