Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ3 ሺህ 600 ሄክታር በላይ የመንግሥት የመሬት ይዞታዎች ዲጂታል ካርታ እየተዘጋጀላቸው ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከ3 ሺህ 600 ሄክታር በላይ ለሚሆኑ የፌደራል መንግሥት የመሬት ይዞታዎች የዲጂታል ካርታ እየተዘጋጀላቸው መሆኑን የፌዴራል የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ።
 
የኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን እንደገለጹት÷ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ4 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በፌደራል መንግሥት ይዞታ ሥር ይገኛል።
 
እነዚህ የመሬት ይዞታዎች በአግባቡ ጥቅም ላይ ያልዋሉ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ÷ ለአገሪቱ መስጠት የሚገባቸውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች እንዳይሰጡ መደረጉንም አስረድተዋል ።
 
በተለይም አንዳንድ ሰፋፊ የመንግሥት የመሬት ይዞታዎች ያለምንም ጥቅም ታጥረውአገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶች ማስወገጃ እስከመሆን መድረሳቸውን ለአብነት ጠቁመዋል።
 
ኮርፖሬሽኑም እነዚህን ይዞታዎች ለሚፈለገው አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የይዞታዎቹን መረጃዎች የማጠናቀር ሥራ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
 
ይህንን ተከትሎም በተለይም በአዲስ አበባ ከ3 ሺህ 600 ሄክታር በላይ ለሚሆኑ የመንግሥት የመሬት ይዞታዎች የዲጂታል ካርታ እየተዘጋጀላቸው መሆኑንም አስረድተዋል።
 
ጎን ለጎንም ይዞታዎቹን ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በመተባበር ወደ ኮርፖሬሽኑ የመሬት ባንክ የማዞር ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
 
በመዲናዋ እስከ 3 ሺህ 800 ሄክታር የመንግሥት የመሬት ይዞታ መኖሩን የተሰበሰቡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ ገልጸው÷ ነገር ግን ይዞታዎቹ ከዚሀ አሃዝ እንደሚልቅ አመላክተዋል።
 
ለቀሪዎቹ ይዞታዎችም አስፈላጊውን መረጃ በማጠናቀር ዲጂታል ካርታ እንደሚዘጋጅላቸው መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.