Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የስልጠና ጥራትን ለማሻሻልና የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራ የሚበረታታ መሆኑን ዓለም ባንክ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴርን በማቋቋም የስልጠና ጥራትን ለማሻሻል እና የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ያደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን በዓለም ባንክ ትምህርት ዘርፍ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ሳፋ ኤል ኮጋሊ ገለፁ።
 
ዳይሬክተሯ የቴክኒክና ሙያና ሥራ ዕድልን አሰመልክተው ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ውይይት አድርጓል።
 
በውይይቱ ሳፋ ኤል ኮጋሊ የኢትዮጵያ መንግስት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴርን በማቋቋም ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ትልቅ ኃላፊነት ሰጥቶ በቴክኒክና ሙያው ዘርፍ ጥራትን ለማስጠበቅ እና ብዙ ሥራዎች እንዲፈጠሩ ያደረገውን ጥረት አድንቀዋል።
 
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የቴክኒክና ሙያ ስልጠናው በሥራ ገበያው የተቃኘ እንዲሆንና ለወጣቶችም የሥራ ፈጠራ አስተሳሰብን ለማስረፅ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት አማካኝነት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
 
የትብብር ሥራቸውን በማጠናከር ለአገሪቱ ዕድገት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ መግለፃቸውን ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.