Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረትን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ከአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ጋር ተወያዩ።
 
በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ገልጻ አድርገውላቸዋል።
 
ከዚህ ባለፈም የአጋሮች ድጋፍ ታክሎበት ኢትዮጵያ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ስለምታደርገው እንቅስቃሴ ማብራሪያ መስጠታቸውን አምባሳደሩ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
 
በተጨማሪም የኢትዮጵያ-ፈረንሳይ / የአውሮፓ ህብረትን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይም ውይይት ተደርጓል።
 
በውይይቱ ላይ በስትራስቡርግ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.