Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ በአቶ አህመድ ሽዴ ከተመራ የፌደራል ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከተመራ የፌደራል መንግስት ልዑካን ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በክልሉ በተከሰተው ድርቅ እና እየተሰጠ ባለው ምላሽ ዙሪያ መምከራቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
በክልሉ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ድርቅ በዘላቂነት ለመከላከልና የህብረተሰቡን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ምክክር አድርገዋል፡፡
 
የውሃ፣ የጤና፣ ግብርናና መሰል አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ በማሟላት፣በክልሉ ያለውን የውሃ እጥረት ችግር በመቅረፍ ዘላቂ መፍትሔ መፍጠር እንደሚገባም ተነስቷል።
 
በመጨረሻም ከፌደራል መንግስት፣ ከዓለም ባንክ፣ ከሀገር አቀፍ እና ለጋሽ የግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የዘላቂ ልማት ፕሮጀክቶችን በማቀድና በመተግበር ዘላቂ መፍትሔ መስጠት በሚቻልባቸው ሀሳቦች ላይ ከስምምነት መደረሱን የሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.