Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል የእንስሳት መኖ የማልማት ስራ እየተከናወነ ነው- አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቀ ሳቢያ በእንስሳት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች የእስሳት መኖ የማልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ገለጹ፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ የከፋ ጉዳት እንዳያደረስ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
በዚህ መሰረትም ድርቁን ተከትሎ በእንስሳት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል የእንስሳት መኖ የማልማት ስራ እየተከናወኑ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
በተለይም በሸበሌ እና ዳዋ ዞኖች ለእንስሳት መኖ የሚውሉ እጽዋቶችን የወንዝ ውሃዎችን በመጠቀም የማልማቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.