Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ ከ605 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት በተያዘው ሳምንት ለነዋሪዎች ይከፋፈላል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ደሴ ከተማን ሙሉ በሙሉ ማዳረስ የሚያስችል ከ605 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት በተያዘው ሳምንት ለነዋሪዎች እንደሚከፋፍል የከተማዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡
 
በመምሪያው የሸማቾች ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ አማረ ጥበቡ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከፌቤላ የዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጋር በመተባበር በተያዘው ሳምንት ለከተማ ነዎሪዎች የዘይት ምርት ይሰራጫል።
 
የዘይት አቅርቦቱ በሸማች ማህበር በኩል እንደሚቀርብ የተናገሩት ቡድን መሪው÷ በገበያው ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመከላከልም የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
 
በዚህ መሰረት በከተማዋ በሸማች ማህበራት በኩል የሚቀርበው የዘይት ዋጋ ፡-
ባለ 3 ሊትር =290 ብር ከ06 ሳንቲም
ባለ 5 ሊትር =474 ብር ከ40 ሳንቲም
ባለ10 ሊትር=936 ብር ከ69 ሳንቲም
ባለ 20 ሊትር =1 ሺህ 834 ብር ከ66 ሳንቲም
ባለ 25 ሊትር=2 ሺህ 277 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ከደሴ ከተማ በተጨማሪ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከሶስት ቀናት በሗላ ለከተማዎ ነዎሪዎች የዘይት ምርት እንደሚያቀርብ ተመላክቷል፡፡
 
ስለሆነም ማህበረሰቡ አላግባብ ወጪ ከማውጣት በመቆጠብ ህገ ወጦችን ለሚመለከተው አካል በመጠቆም እንዲተባበር የንግድና ገበያ ልማት መምሪያው ጥሪ አቅርቧል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.