Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ቤተሰቦች የጤና መድህን አገልግሎት አግኝተዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በስድስት ወር ከ1 ነጥብ 1ሚሊየን በላይ አባወራዎች እና እማወራዎችን የጤና መድህን አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረጉን በኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ሃላፊ አቶ ደረጄ አበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፥ ኤጀንሲው ከአባልነት መዋጮ አሰባሰብ ጋር በተያያዘ ከ199 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብስቦ ወደ ባንክ ማሳደጉን ሃላፊው ተናግረዋል።

ኤጀንሲው አገልግሎቱን በምስራቅ ሐረርጌ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየሰጠ ይገኛልም ነው ያሉት።

በዚህም በምስራቅ ሐረርጌ የጤና መድህን አባል ይሆናሉ ከተባሉ 700 ሺህ ቤተሰቦች መካከል 580 ሺህ ቤተሰቦችን አባል በማድረግ የዕቅዱን 82 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል።

በተመሳሳይ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 59 ሺህ 523 ቤተሰቦች አባል ይሆናሉ ተብሎ ተጠብቆ 31 ሺህ 310 ቤተሰቦች አባላት ማፍራት ስለመቻሉ ተጠቁሟል።

በሐረሪ ክልል በዚህ ዓመት 45 ሺህ 338 አባወራዎች እና እማወራዎች አባል ለማድረግ ታቅዶ ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ ማሳካት ስለመቻሉ ተገልጿል።

ኤጀንሲው በራሳቸው ከፍለው መታከም ለማይችሉ ቤተሰቦችች በአጠቃላይ ከ42 ሚሊየን በላይ ክፍያን ለጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች ክፍያ መፈፀሙን አስታውቋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.