Fana: At a Speed of Life!

በአገር አቀፍ ደረጃ ዘንድሮ በ400 ሺህ ሄክታር መሬት የበጋ ስንዴ ምርት ልማት እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገር አቀፍ ደረጃ ዘንድሮ በ400 ሺህ ሄክታር መሬት የበጋ ስንዴ ምርት ልማት እየተከናወነ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።
በሚኒስቴሩ የሰብል ልማት ዳይሬክተር ኢሳያስ ለማ እንደገለጹት÷ በአስር ዓመት መሪ የልማት እቅድ ስንዴን በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት እቅድ ተይዟል።
ይህን ተከትሎም ባለፉት ሁለት ዓመታት ከውጭ የሚገባውን የስንዴ ምርት በአገር ውስጥ ለመተካት ከባለኃብቶችና ከአርሶ አደሩ ጋር በመተባበር ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
የስንዴ ምርት ቀደም ሲል በክረምት ወቅት የሚለማ መሆኑን አስታውሰው አሁን ላይ ዓመቱን ሙሉ ለማልማትና ምርቱን ለመጨመር የበጋ ወቅትን መጠቀም አስፈልጓል ብለዋል።
የበጋ ስንዴ ልማት ሥራዎች አምና ለስንዴ ምርት ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን 180 ሺህ ሄክታር አሁን ላይ 400 ሺህ ሄክታር መድረሱን የተናገሩትዳይሬክተሩ ÷በዚህ የእርሻ መሬት 16 ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን አመላክተዋል።
 
ሌላው የመስኖና ቆላማ አካባቢዎችን አሟጦ በመጠቀም ረገድ ሦስት አማራጮች ተዘጋጅተው በዚሁ መሰረት በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በመስኖ አምራች ያልነበሩ አካባቢዎች ወደ ምርት እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.