Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ለመንገድ አገልግሎት የተቀመጠ ድማሚት ፈንድቶ የ7 ህጻናት ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ግራር ውኃ በተባለ ቀበሌ ለመንገድ አገልግሎት የሚውል ድማሚት ፈንድቶ የ7 ህጻናት ህይወት ማጥፋቱን የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ኃይሌ ብርሃኑ እንደገለጹት÷ አደጋው የተከሰተው የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ገደማ ነው።
አደጋው የተከሰተው በሱር ኮንስትራክሽን ሲሰራ በነበረ የመንገድ ፕሮጀክት የቁሳቁስ ካምፕ ላይ ሲሆን÷ በዚህ ውስጥም የአካባቢው ህጻናት ለጨዋታ ሲገቡና ሲወጡ እንደነበር መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.