Fana: At a Speed of Life!

ከቱሉ ዲምቱ እስከ ቃሊቲ አደባባይ ሲሰራ የነበረው የውሃ መስመር የማዛወር ስራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንገድ ሥራ ምክንያት ከአቃቂ ክፍል 1 ወደ ከተማ ውሃ ይዞ የሚመጣውና 18 ነጥብ 94 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ከፍተኛ የውኃ መስመር ማዛወር ሥራ ተጠናቆ ለመንገድ ስራው ክፍት ተደርጓል፡፡
የመስመር ማዛወር ሥራው በ48 ሚሊየን 876 ሺህ 163 ነጥብ 72 ብር እና በ7 ሚሊየን 245 ሺህ 883 ነጥብ 4 የአሜሪካ ዶላር ወጪ በአሰር ኮንስትራክሽን ኃ.ግ.ድ እና በ አይ ኤፍ ኤች ኮንስትራክሽን አማካኝነት ነው ተሠርቶ የተጠናቀቀው፡፡
የከፍተኛ የውኃ መስመር ማዛወር ሥራው ባለ 800፣ ባለ 400 እና ባለ 250 ሚሊ ሜትር ስፋት ያላቸውን መስመሮች ያካተተ ሲሆን ውኃውን ከነባሩ መስመር በተሳካ ሁኔታ ማዛወር መቻሉን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የላከው መግለጫ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.