Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች የቅድመ ጉባዔ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች የቅድመ ጉባዔ ውይይት በአዳማ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

 

በጉባዔ ዝግጅት ሂደት በተካሄዱ ሀገር አቀፍ የፓርቲ ኮንፍረንሶች መላው የብልፅግና ፓርቲ አባላት በጉባዔው በቀጥታ በመሳተፍ የሚወክሏቸውን መምርጣቸው ይታወቃል፡፡

እነዚህ ውክልና የተሰጣቸው የጉባኤ አባላት በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ ውይይት እያካሄዱ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የቅድመ ጉባዔ ውይይቱ እስከ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን÷ በጉባዔ ሪፖርት እና በቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ሪፖርት እንዲሁም በፓርቲው ህገ ደንብና ፕሮግራም ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡

ውይይቱን ያስጀመሩት የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ባደረጉት ንግገር÷ የቅድመ ጉባዔ ውይይቱ በፓርቲው አመራር ሀገራችን ስኬቶች ባስመዘገበችበት ወቅት እና በበሳል አመራር ሰጪነት ልንፈታቸው በሚገቡ ሀገራዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነን የምናካሂደው ነው ብለዋል፡፡

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰጠንን ኃላፊነት እና እምነት ከዳር ለማድረስ በወንድማማችነትና አብሮነት መንፈስ መስራት ይገባናል ያሉት አቶ አደም÷ በቅድመ ጉባዔ የሚካሄደው ይህ ውይይት ለአንደኛ ጉባዔያችን ስኬታማነት ቁልፍ አስተዋፅኦ አለው ነው ያሉት፡፡

በውይይቱ 1 ሺህ 600 ጉባኤተኞች እየተሳተፉ መሆናቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.