Fana: At a Speed of Life!

በጦር ግንባር ጀብድ የፈፀማችሁ ሴቶች ላመጣችሁት ድል እጅግ እናመሰግናለን- ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በናንተ ድርብ መስዋዕትነት ሀገር ትቀጥላለች፤ ለናንተ ክብር መስጠት ያስፈልጋል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች ኤይት) በተለያዩ ዝግጅቶች በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተከበረ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ባደረጉት ንግግር÷ በጦር ግንባር ጀብድ የፈፀማችሁ ሴቶች ላመጣችሁት ድል እጅግ እናመሰግናለን፤ የሀገራችን ሰላም በሴቶች ተጋድሎ ይረጋገጣል፤ በጀግና ሴቶች ሰማዕትነት ሀገራችን ታፍራ እና ተከብራ ትኖራለች ብለዋል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ በከፈተው በጦርነት ላይ ትልቅ ሚና የነበራቸውና ታሪክ የፃፉ የሴት መከላከያ ሰራዊት አባላት የምስጋና እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በብዙ ችግር ውስጥ ሆነው የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ግንባር መዝመታቸው ለእኛ ትልቅ ክብር ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ÷ በጦርነቱ ያጣናቸውን ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም ሁሌም እናወሳቸዋለን ብለዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ111ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ በሚከበረው የሴቶች ቀን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የሰራዊቱ አመራሮች ተገኝተዋል።
ቀኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ “እኔም የእህቴ ጠባቂ ነኝ!!” በመከላከያ ደግሞ “የሀገራችን ሰላም በሴቷ ተጋድሎ ህያውነት ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው፡፡

በቅድስት ተስፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.