Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኮይካ የ20 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ መካከል የ20 ሚሊየን ዶላር የዕርዳታ ስምምነት የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ።

የእርዳታ መግባቢያ ሰነዱ የተፈረመው የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ የ2022 የድጋፍ መርሃ ግብር ማስፈጸሚያ ማዕቀፎችን፣ የኢትዮጵያን የአሥር ዓመት ዕቅድ እና ዘላቂ የልማት ግቦችን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያን የልማት ጥረት ለማሳካት በሚያግዝ መልኩ ነው።

የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ÷ አዲስ በቀረፀው የኢትዮጵያ የልማት ዕቅድ ድጋፍ የሚሆን የ20 ሚሊየን ዶላር በጀት ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ ተግባራዊ ለሚደረጉ ሁለት ፕሮጀክቶች አጽድቋል፡፡

እያንዳንዱ ፕሮጀክት 10 ሚሊየን ዶላር ተይዞለታል ነው የተባለው፡፡

የመጀመሪያው ፕሮጀክት በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ዘርፍ ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ምርትና ምርታማነት ለማጎልበት የሚውል ሲሆን÷ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግና የተደላደለ የገበያ እና የንግድ ትሥሥር ለማዳበር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

ሁለተኛው ፕሮጀክት ደግሞ በኢትዮጵያ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ማኅበራዊ ትሥሥራቸውን እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን ለማጎልበት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መቋቋምን ለመፍጠር፣ ቀጣይነት ያለው የኑሮ መሻሻልን ለማሳደግ እንዲሁም ዘላቂ ሠላም ለማምጣት የሚያግዝ ነው፡፡

የመግባቢያ ሠነዱን የተፈራረሙት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ሊ ባይንግዋ መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስትር መረጃ አመልክቷል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.