Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያ ለሊቢያ ሰላም ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሊቢያ ከፍተኛ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ካሊድ አል-ሚሽሪ እና ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ ለሊቢያ በዓለም አቀፍ እንዲሁም ክልላዊ ተቋማት አማካኝነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።

ሊቢያውያን በሀገራቸው ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ እንዲበረቱና በአንድነት ጥረት እንዲያደርጉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ሊቀ-መንበሩ ካሊድ አል-ሚሽሪ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሰላም ሽልማትን በማግኘታቸው ደስታቸውን በመግለፅ በአመራራቸው ያስገኟቸውን ለውጦች አስመልክቶ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

እንዲሁም በሊቢያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለሚደረገው ቀጣይ ጥረት እገዛ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.