Fana: At a Speed of Life!

ሳፋሪኮም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በተገነቡት መሰረተ ልማቶች ደስተኛ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ሳፋሪኮም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የተገነቡት መሰረተ ልማቶች ዓለም ዓቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸው በፓርኮቹ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዲያድርበት ማድረጉ ተገለፀ፡፡
በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ዋና ስራ አስፈጻሚ የተመራ ልዑክ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እንደተናገሩት ፥ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለሳፋሪኮም እንዲሁም ለሌሎች ዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ኩባንያዎች ምቹ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን አስታውሰው ፥ ሳፋሪኮም በፓርኮቹ ጉብኝት በማድረግ እነዚህን አማራጮች በጥልቀት እንዲመለከት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሳፋሪኮም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብቶ መስራት ፓርኮች እስካሁን በብዛት ሲሰሩበት ከነበረው የቴክስታይል ዘርፍ የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግና የቢዝነስ ዘርፎችን ለማካተት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ውጤታማ ያደርገዋል ያሉት አቶ ሳንዶካን ኮርፖሬሽኑ ከሳፋሪኮም ጋር በተለያዩ ዘርፎች አብሮ ለመስራት እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ያለውን ፍላጎት በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሱሳ በበኩላቸው ፥ ከኮርፖሬሽኑ ጋር አብሮ የመስራት እድል ስለመገኘቱ አመስግነው ፥ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በተለይም በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ዳታ ሴንተር የመገንባትና፣ በሌሎች ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ሌሎች ፕሮጀክቶችን የመተግበር ፍላጎት እንዳለው አሳውቀዋል፡፡
በተጨማሪም ዋና ስራ አስፈፃሚው ፥ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ብሎም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለው የስራ እንቅስቃሴ ጅማሮ መሆኑን ገልጸው ፥ እጅግ ትልልቅ የተቋሙ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ ወደፊት ተግባራዊ ይደረጋሉ፤ ለዚህም ሳፋሪኮም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ ነው ማለታቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.