Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለአፋርና አማራ ክልሎች 250 ሜትሪክ ቶን የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ መንግሥት በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) በኩል በአፋርና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 250 ሜትሪክ ቶን የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
 
ለክልሎቹ የተደረገው ድጋፍ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ግምት ያለው ምግብ ነክ ያልሆነ ቁሳቁስ ነው ተብሏል፡፡
 
ድጋፉ በአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና በዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት በኩል ለተጎጂዎች ይደርሳልም ነው የተባለው፡፡
 
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ድጋፉን በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነሲቡ ሁሴን ማስረከባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.