Fana: At a Speed of Life!

በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወርና ተከማችቶ የተገኘ ከ110 ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይትና 95 ኩንታል ስኳር ተያዘ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ ወጥ መንገድ ሲራገፍ የተገኘ 50 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት እና በሶስት መጋዘኖች የተከማቸ 60 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይትን ጨምሮ 95 ኩንታል ስኳር በተለያዩ ከተሞች ተይዟል፡፡

50 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይቱ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 29490 ኢ.ት ተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ በሐረር ከተማ ሃማሬሳ አካባቢ በሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሲያራግፍ መገኘቱን የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቡሽራ አልይ ተናግረዋል።

በጭነት ተሽከርካሪው ላይ ከነበረው ግማሽ ያህሉ የምግብ ዘይት ተራግፎ ወደ መጋዘን እንደገባና ቀሪው እንደተጫነ መገኘቱንም ነው ሃላፊው የገለጹት።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ከሌሎች የህግ አስከባሪዎች ጋር በመሆን በተደረገው ክትትል በህገ ወጥ መንገድ የተገኘውን የምግብ ዘይት መያዝ እንደተቻለ የገለጹት አቶ ቡሽራ÷ አሽከርካሪው ለጊዜው ከአካባቢው መሰወሩን ጠቁመዋል።

የተያዘው ዘይትም የጽህፈት ቤቱ ማኔጅመንት ተወያይቶ በሚወስነው መሰረት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚከፋፈል መናገራቸውን ከሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ሮቤ ከተማ አስተዳደር በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 60 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት እና 95 ኩንታል ስኳር በሕገ ወጥ መንገድ በሶስት መጋዘኖች ተከማችቶ መገኘቱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.