Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ 51 ቤቶች ወደሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በደላንታ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ 51 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን የወረዳው አስተዳደር ገለጸ።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ፥ የእሳት አደጋው የደረሰው በጥንቃቄ ጉድለት ከአንድ ቤት በተነሳ ቃጠሎ መሆኑን ገልጸዋል።

በአደጋው የሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም 18 አባወራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

አደጋው በወረዳው 016 ቀበሌ መከሰቱን የገለጹት አሰተዳዳሪው ፥ በመኸር ወቅት የደረሰና ወደ ቤት የገባ የእህል ምርት ሙሉ በሙሉ መውደሙንም ተናግረዋል።

የወረዳው አስረተዳደር በአካባቢው ያለውን ችግር ለመመልከትና መረጃዎችን በመሰብሰብ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ አጣሪ ግብረ ኃይል ወደ ቦታው መላኩን አቶ አያሌው ተናግረዋል።

አደጋው ተናንት ከቀኑ በ5:30 ላይ መከሰቱንም ነው የወረዳው አስተዳዳሪ የገለጹት።

በከድር መሀመድ

ፎቶ ፡- ከኮሙኒኬሽን ቢሮ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.