Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡
 
ኢንስቲትዩቱ ከዴንማርኩ ኮፐንሀገን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል።
 
በዳሰሳ ጥናቱ የመጀመሪያ ግኝቶች ላይ በዛሬው ዕለት ውይይት እየተደረገ ሲሆን÷ ጥናቱ የተካሄደው በ5 ክልሎች እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ነው ተብሏል።
 
በጥናቱ ከተካተቱት ቤተሰቦች ውስጥ 24 በመቶ የሚሆኑት ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 1 ጊዜ ድርቅ እንዳጠቃቸው ጥናቱ አመላክቷል።
 
ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚተዳደርበት የግብርናው ዘርፍም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖው እየበረታ እንደሆነ መገለጹን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
በአሁኑ ወቅት በምስራቅና በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በርካታ ዜጎች ለድርቅ መጋለጣቸውም ተጠቅሷል።
 
እ.ኤ.አ. ከ1965 እስከ 2015፣ ከ15 የሚበልጡ ድርቆች በኢትዮጵያ መከሰታቸውም ተገልጿል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.