Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ እና ዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቱርክ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ እና ዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ እና በቀጠናው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ታሳቢ ያደረገ ውይይት ዛሬ በቱርክ አንታሊያ ማካሄድ ጀምረዋል፡፡
 
በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት የሚካሄደው ይህ ውይይት÷አገራቱ ግጭት ውስጥ ከገቡ ወዲህ በከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል የሚደረግ የመጀመሪያው ምክክር ነው ተብሏል፡፡
 
የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፥ ውይይቱ ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በዘለለ ጦርነቱን እንዴት እና በምን ሁኔታ ማቆም እንደሚቻል የመፍትሄ ሃሳብ የሚሰጥበት ወሳኝ ስብሰባ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡
 
የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በበኩላቸው÷ ውይይቱ ለዘለቄታዊ የተኩስ አቁም ስምምነት በሮችን ይከፍታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው መግለጻቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡
 
ቱርክ የሁለቱን አገራት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማመቻቸት እና የቀጠናውን ሰላም ለማስጠበቅ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከአገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ወሳኝ ምክክር በማድረግ የአደራዳሪነት ሚናዋን ትወጣለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.