Fana: At a Speed of Life!

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማኅበር የ82 ሺህ 610 የአሜሪካ ዶላር ቦንድ ግዢ ፈፀመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማኅበር ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ የ82 ሺህ 610 የአሜሪካ ዶላር ቦንድ ግዢ ፈፀመ፡፡

ማኅበሩ የዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ መካሄዱን ተከትሎ ከፍተኛ ደስታ የተሰማው መሆኑን በመግለጽ የ82 ሺህ 610 የአሜሪካ ዶላር የቦንድ ግዢ መፈጸሙ ተገልጿል፡፡

በቦንድ ግዢው ስነ-ስርዓት በጂቡቲ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሀኑ ፀጋዬ ባደረጉት ንግግር÷ ማኅበሩ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ እያደረገ ያለውን ተከታታይ ተሳትፎ አድንቀዋል፡፡

ይህ ተሳትፎ በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትየጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውን በአገራዊ ጥሪዎች ላይ የሚያደርጉትን ርብርብ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ማህበሩ በሀገሪቱ ለሚያደርገው ሁለንተናዊ ልማት አባላቱን በማስተባበር ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ማህበሩ እና የማህበሩ ሰራተኞች በየዓመቱ የቦንድ ግዢ ሲፈጽሙ እንደቆዩ የገለጹት የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ንጉሴ ሀይሌ÷ቀደም ብለውም ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለተፈናቀሉ ወገኖችና ለሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ይህንን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው÷ማህበሩ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ የ207 ሺህ 610 የአሜሪካ ዶላር የቦንድ ግዥ ፈጽሟል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.