Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከፊንላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከፊንላንድ አምባሳደር ሆሎፔነን ኦቲ ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትሩ የፊንላንድ መንግስት በትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፕሮግራም እና በልዩ ፍላጎት አካታች ትምህርት ላይ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት በሚፈለገው ደረጃ ላይ ባለመድረሱ ጠንካራ ስራ መስራት እንደሚጠይቅ የጠቀሱት ሚኒስትሩ በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በተሻለ እና ደረጃውን በጠበቀ ዲዛይን ለመገንባት እንደታቀደና በዲዛይኑ ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያም ገለፃ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ የፊንላድ አምባሳደር ሆሎፔነን ኦቲ በበኩላቸው አገራቸው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም በመዘርጋቷ የትምህርት ጥራት እንዲኖርና የትምህርት ስርዓቱ ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ እገዛ እንዳደረገ ገልፀዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚደረጉ የሁለትዮሽ ትብብር ስራዎች በዋናነት የትምህርት ፍትሃዊነት እና አካታችነት ትኩረት የሚሰጥባቸው ተግባራት ሲሆኑ የመምህራን ስልጠናን እንደሚያካትት መናገራቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የትምህርት ቤቶች ምገባን ለማጠናከርና ለአደጋ ጊዜ ትምህርት ፕሮግራም የሚውል 3 ሚሊየን ዩሮ እርዳታ መሰጠቱን ጠቅሰዋል።

በቀጣይ በቅርብ በሚዘጋጀው የሁለትዮሽ ትብብር ስምምነት ሰነድ ላይ የትምህርት ዘርፉ የጥራት ሪፎርም ስራዎች ትኩረት ይሰጣቸዋል ተብሏል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.