Fana: At a Speed of Life!

2ኛው የአፍሪካ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው የአፍሪካ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፎረም እና 6ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ፎረም በዚምባቡዌ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ፎረሙ “በመጪው አስር ዓመታት በብልጽግና የምትለወጥ አፍሪካ” በሚል መሪ ቃል ነው በቪክቶሪያ ፎልስ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው፡፡

እስከ መጪው ሃሙስ በሚቆየው ፎረም ላይም ኢትዮጵያ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመወከል እየተሳተፈች ይገኛል፡፡

ፎረሙ በአፍሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘላቂ ልማት ግቦች እና የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ ዙሪያ ያሉ እንቅስቃሴዎችን መገምገም እና መልካም ተሞክሮዎችን መለዋወጥ ላይ አላማ ያደረገ ነው፡፡

እንዲሁም በፎረሙ ማጠቃለያ የሚለዩ ምክረ-ሀሳቦችን ወደ ፊት ለሚካሄዱ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ግቦች፣ የመሪዎች ፎረም እና ለዓለም የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፎረም ማቅረብ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.