Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ መረጃቸውን በማስተካከል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵ ንግድ ባንክ  ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ መረጃቸውን  በማስተካከል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡

ባንኩ ዛሬ በሰጠው ማብራሪያ÷ ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ መረጃቸውን በማስተካከል አገልግሎት ማግኘት እንድሚችሉ አስታውቆ በዛሬው ቀን በቅርንጫፎች የተፈጠረው መጨናነቅ አላስፈላጊ መሆኑንም ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አ.ኤ.አ በ27/08/2021 ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ  የደንበኞችን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ስራ ላለፉት 6 ወራት በመሥራት ላይ መሆኑን አስታውሷል፡፡

በዚህም መሠረት÷ እስካሁን በርካታ ደንበኞች መረጃቸውን በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወቅታዊ ማድረጋቻውን አስታውቋል፡፡

ሆኖም እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ያልቻሉ ደንበኞች÷  የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አግልግሎቶች ብቻ ማለትም  (የሞባይል ባንኪንግ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ እንዲሁም የኤቲኤም እና የፖስ አገልግሎት) እንደሚቋረጥባቸው ገልፆ÷ በማንኛውም ጊዜ ግን  ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች በመምጣት መረጃቸውን ሲያስተካክሉ ወዲያውኑ አገልግሎቶችን ማግኘት  እንደሚችሉም አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ የማህበራዊ ትሥሥር ገጾች እና የመረጃ ምንጮች መረጃ ያላስተካከሉ ደንበኞች ሂሳብ ይዘጋል በሚል የሚናፈሰው ወሬ በፍጹም ትክክል አለመሆኑን ባንኩ አረጋግጧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.