Fana: At a Speed of Life!

ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና በመጫወት የአዲስ ምዕራፍ ጅማሮን እውን ያደርጋሉ ብዬ አምናለሁ – የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና በመጫወት በኢትየጵያ ታሪክ የአዲስ ምዕራፍ ጅማሮን እውን ያደርጋሉ ብዬ አምናለሁ አሉ ዶክተር ራሄል ባፌ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ።

የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ በብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት÷በሀገሪቱ የተቋቋመው የምክከር ኮሚሽን ዓላማውን ገለልተኛ ሆኖ ያሳካ ዘንድ ገዢው ፓርቲ ብልፅግና ፓርቲ ልዩ ዓላፊነት እንዳለበት ጠቁመዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት የነበሩ ችግሮችን አልፈን ይህንን መርሀ ግብር በጋራ ለመታደም በመብቃታች እድለኞች ነን ብለዋል፡፡

ራዕያችን ዲሞክራሲያዊ የሆነች ፣ የተረጋጋች፣ ሰላም የሰፈነባት፣ ለሁላችን እኩል ሆነች ሀገር መገንባት ነው ያሉት ዶክተር ራሄል ባፌ ፥ ሀገራችንን እና ህዝባችንን የመታደግ ሃላፊነት በእጃችን ነው ብለዋል፡፡

እኔ ከሚል አስተሳሰብ ወጥተን ተሸንፈን የምናሸንፍበት ዕድል በእጃች ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አይሆንም አይሳካላቸውም የተባልነውን ፥ ማሳካት አይችሉም የተባልነውን ፥ አሳክተንም አነጋጋሪ ስኬት የምናስመዘግብበት እድል በእጃችን ነው ብለዋል የጋራ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ማጠናከርና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ሃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚያግዝ ተቋም እንደሆነ ገልፀው፥ አስተማማኝ የፖለቲካ መረጋጋት ሰፍኖ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ለማስቻል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ነው የገለጹት፡፡

በመሆኑም ለሀገራዊ የጋራ ጉዳዮች ፣ በዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ፣ የሕግ የበላይነትን በሚያግዙ ጉዳዮች ላይ ሃላፊነታቸውን በተጠየቂነት መንፈስ እየተወጡ ይገኛሉም ብለዋል፡፡

ሊፈቱ ባልቻሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመመካከር አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በዝግጅት ላይ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ራሄል፥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ምክክሩን ለማሳካት በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክሩ የሁሉንም ተሳትፎ እንደሚጠይቅም ጠቁመዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.