Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራቷን እንደምትቀጥል የአገሪቱ ኤ ኬ ፒ ፓርቲ አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል የቱርኩ ኤ ኬ ፒ ፓርቲ የውጭ ጉዳዮች ምክትል ሊቀመንበር ፌቭዚ ሻንቨርዲ ገለፁ፡፡
 
የቱርክ ገዥ ፓርቲ የውጭ ጉዳዮች ምክትል ሊቀመንበር በብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እና ቱርክ ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አውስተው፥ ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር በመገናኘት ውይይት ማድረጋቸውንና በአፍሪካ-ቱርክ ጉባኤ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሳተፋቸውን አውስተዋል፡፡
 
ኢትዮጵያና ቱርክ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን የተናገሩት ምክትል ሊቀመንበሩ፥ በትምህርት፣ በወታደራዊ እና በንግድ ትስስር ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
 
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላም እንዲፈታም ሁለቱ ወገኖች ወደ ውይይት እንዲመጡ ቱርክ ድጋፍ እንደምታደርግ ነው የፓርቲው የውጭ ጉዳዮች ምክትል ሊቀመንበር ፌቭዚ ሻንቨርዲ ፌቭዚ የገለጹት፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.