Fana: At a Speed of Life!

እንደ እህትማማች ሀገራት በጋራ ለማደግ ግንኙነታችንን የበለጠ ለማጠናከር በጋራ መስራት አለብን – የጅቡቲ እና ኡጋንዳ እህት ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደ እህትማማች ሀገራት በጋራ ለማደግ ግንኙነታችንን የበለጠ ለማጠናከር በጋራ መስራት አለብን ሲሉ የጅቡቲ እና ኡጋንዳ እህት ፓርቲዎች ገለጹ፡፡
 
የጅቡቲው “ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ” ፓርቲ ዋና ፀሐፊና የሀገሪቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ኢልያስ ሙሳ ዳዋሌ በብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ጅቡቲ እና ኢትዮጵያ በደም የተሳሰርን እህትማማች ሀገራት እንደመሆናችን በጋራ ለማደግ የቅርብ ግንኙነታችንን የበለጠ አጠናክረን ማስጠቀል አለብን ሲሉ ብለዋል፡፡
 
ጅቡቲ እና ኢትዮጵያ ለረዥም ዓመታት ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው እና በደም የተሳሰሩ እና ተመሳሳይ ባህል የሚጋሩ ህዝቦች ያሉባቸው ሀገራት በመሆናቸው በጋራ ለማደግ ጠንካራውን ዝምድናቸውን የበለጠ አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
 
ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያውያንን ዘርፈ ብዙ ፍላጎት እየመለሰ ያለ እና ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ አበረታች እንቅስቃሴ ያደረገ ፓርቲ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
 
የዩጋንዳው ገዢ ፓርቲ ናሽናል ሪዚዝታንስ ሙቭመንት ምክትል ሊቀመንበር አልፐር ሲሞን ፒተት በበከላቸው ÷ሁለቱ ሀገራት ለጋራ እድገትና ብልጽግና እንዲሁም የዜጎቻቸውን ሁለንተናዊ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
 
ፓርቲያቸው ናሽናል ሪዚዝታንስ ሙቭመንት እና ብልጽግና ፓርቲም የሚያመሳስላቸው የጋራ እሴቶች ስለአሏቸው ለጋራ እድገት እና ብልጽግና በጋራ ይሰራሉ ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፡፡
 
ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሴቶችን ለሃላፊነት እንዲበቁ በማድረግ በኩልም ተመሳሳይ አበረታች ስራዎች እንደሰሩ አስገንዝበዋል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.