የብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ አስከሬን የሽኝትና የቀብር ስነ-ስርዓት የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስከሬን ሽኝትና ለቀብር ስነ ስርዓት ዝግ የሚሆኑና ተለዋጭ መንገዶችን ይፋ ማድረጉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡
የሽኝቱና የቀብር ስነ-ስርዓቱ በሰላም እንዲከናወን የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡
ቅዳሜ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የፓትርያርኩ አስከሬን ሽኝት የሚካሄድና የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ይሆናል፡፡
ነገ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄደው የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ዝግ የሚሆኑና ተለዋጭ መንገዶችን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡
በዚሁ መሠረትም፡-
ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ
ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ
ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት
ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል መብራት
ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር
ከጦር ኃይሎች ፣ በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከቀኑ 12:30 ጀምሮ ዝግጅቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡
በዕለቱምየብፁእነታቸው አስከሬን ከመስቀል አደባባይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ (ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን) በሚንቀሳቀስበት ወቅት ከመስቀል አደባባይ ፣ በብሔራዊ ቤተ መንግስት፣ ውጭ ጉዳይ ፣ አራት ኪሎ፣ ቅድስት ማርያም የሚወስደው መንገድ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ስነ-ስርዓት የሚፈፀም በመሆኑ የቀብር ስነ-ስርዓቱ እስከሚፈፀም ወደ ቅድስት ማርያም፣ አራት ኪሎ እና ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሰጡት አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ለጋራ ደህንነት ሲባል በሽኝቱ እና በቀብር ስነ-ስርቱ ወቅት ፍተሻ መኖሩን የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ተገንዝበው ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳስቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!