Fana: At a Speed of Life!

በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል በተደረጉ ውይይቶች አወንታዊ ለውጦች ታይተዋል – ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል የተደረጉ ሶስት ወይይቶች ያለስምምነት ቢጠናቀቁም አወንታዊ ለውጦች መታየታቸውን የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፡፡
 
ፕሬዚዳንቱ ከቤላሩሱ አቻቸው አሌክሳንደር ሎካሼንኮ ጋር በነበራቸው ውይይት እንደተናገሩት፥ባለፉት ጊዜያት በተደረጉ ውይይቶች መልካም የሚባሉ ለውጦች ታይተዋል፡፡
 
በሞስኮ እና በሚንስክ መካከል ያለውን ከፍተኛ ትብብር ያደነቁት ፕሬዚዳንት ፑቲን፥በዩክሬን ዙሪያ ስላለው ሁኔታ እና በቀጣይ የሚካሄዱ ድርድሮችን በተመለከተ ለፕሬዚደንት ሎካሼንኮ እንደሚያሳውቋቸው ገልፀውላቸዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንት ሎካሼንኮ እያደረጉት ያለው ፖለቲካዊ ለውጥ ለቤላሩስ የኢኮኖሚ እድገት የሚጠቅም እና ሀገሪቱ እንድትረጋጋ የሚያግዝ መሆኑንም በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ፑቲን ጠቅስዋል፡፡
 
ሩሲያ እና ቤላሩስ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ በማለፍ ሉዓላዊነታቸውን የሚያስከብሩ ሀገራት እንደሚሆኑም እርግጠኛ ነኝ ሲሉ ፑቲን መናገራቸውን ፕሬስ ቲቪ ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.