Fana: At a Speed of Life!

የሰውን ልጅ መልካም ስራና ምግባር እንደሚያስከብረው ከብፁዕነታቸው መማር ይገባል ሲሉ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰውን ልጅ መልካም ስራና ምግባር እንደሚያስከብረው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ መማር ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ገለጹ።
የሰውን ልጅ የሚያስከብረው ስራው፣ ጥረቱ እና እዝነቱ በመሆኑ መልካም ተግባርን ብቻ ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የአስክሬን ሽኝት መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ÷ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
የመለያየትን ኃሳብ በመተው በአንድነትና መከባበር ግድያና ማፈናቀልን ማስቆም እንደሚገባ ጠቁመው÷ ከመንግስት ጀምሮ የሃይማኖት አባቶቹ ክርስቲያን ሙስሊሙ፣ በመዋደድ በመከባበር ግድያና መፈናቀልን እንዲያስቆሙም ጥሪ አቅርበዋል።
በሽኝት መርሃግብሩ የሀገር ውስጥና ከዓለም አቀፍ ኃይማኖት ተቋማት የተወከሉ የየእምነቱ መሪዎች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.