Fana: At a Speed of Life!

የአማራ እና ትግራይ ህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ እየተካሄደ  ነው

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ እና የትግራይ ህዝቦችን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በመርሃ ግብሩ ሁለቱ ህዝቦች ያላቸውን ሁለንተናዊ ትስስር ለማጠናከርና የህዝቦቹን ግንኙነት በማሳደግ ረገድ የምሁራን ሚና በስፋት ይዳሰስበታል ተብሏል።

የሰላም ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ለሃገር ግንባታ በሚጠቅሙ ሃሳቦች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግም ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.