Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሩፒያህ ባንዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሩፒያህ ባንዳ በ85 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ሩፒያህ ከፈረንጆቹ 2008 እስከ 2011 የዛምቢያ ፕሬዚዳንት በመሆን ሃገራቸውን መርተዋል።
ከዚያ ቀደም ብሎ በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ህይወታቸው ያለፈው የሃገሪቱ መሪ ሌቨየ ምዋንዋሳ ምክትል በመሆን አገልግለዋል።
በፈረንጆቹ 2011 በሃገሪቱ በተደረገው ምርጫም በተቀናቃኛቸው ሚካኤል ሳታ መሸነፋቸው ይታወሳል።
በወቅቱም የምርጫ ውጤቱን ያለ ተቃውሞ በመቀበላቸው ከበርካቶች ሙገሳን ተችረው ነበር።
በስልጣን በነበሩበት ዘመን ከሙስና ጋር በተያያዘ ውንጀላ ይቀርብባቸው የነበረ ሲሆን፥ በፈረንጆቹ 2013ትም በርካታ ሚሊየን ዶላሮችን መዝበረዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸው የሚታወስ ነው።
ሩፒያህ ባንዳ በአንጀት ካንሰር ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሕይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.