Fana: At a Speed of Life!

በቆላድባ ከተማ በገበያ ቦታ ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ቆላድባ ከተማ በገበያ ቦታ ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
የቆላድባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ግዛቸው አዳነ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ አደጋው የደረሰው በቀበሌ 1 የገበያ ማዕከል ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ ነው፡፡
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን የገለጹት ከንቲባው፥ 8 የእህል መጋዘኖች እና የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ብለዋል፡፡
በሰው ሕይወት ላይ ያጋጠመ ጉዳት አለመኖሩን ገልጸው÷ አጠቃላይ የደረሰው የጉዳት መጠን በኮሚቴ ተጣርቶ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመድኅን ደምለው እንደተናገሩት÷ በወቅቱ የደረሰው የእሳት አደጋ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በተሠራው የቅንጅት ስራ የእሳት አደጋው በቁጥጥ ስር ውሏል ብለዋል፡፡
ማህበረሰቡም አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጉንም ነው የፅህፈት ቤት ኃላፊው የገለጹት፡፡
በምናለ አየነው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.