Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ዶክተር ዐቢይ አሕመድን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ዶክተር ዐቢይ አሕመድን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።
ትናንት አንደኛ ጉባኤውን የጀመረው ፓርቲው ዛሬ ባካሄደው ምርጫ ዶክተር ዐቢይ አሕመድን የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት በማድረግ መርጧል።

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ÷ “ለጉባኤው እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ከተደመራችሁ ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች“ ብለዋል፡፡

“ክቡር አቶ አደም ፋራህ ዋና እና አጋር የሚለው ግንብ ፈርሶ ሶማሌ ከአጋርነት ወደ ብልጽግና መሪነት በተዋጽኦ ሳይሆን በብቃት የምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታ በማግኘታቸው እጅግ ከፍተኛ ክብር የተሰማኝ መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁም” ነው ያሉት።

“ኢትዮጵያዊ ሆኜ ሁላችሁንም በታማኝነት ሳላዳላ ለማገልገል እንድችል ጊዜና ሁኔታ ወደዚህ ወደዚያ እንዳይወስደኝ በጨዋነትና በትጋት ማገልገል ስለምፈልግ ጸልዩልኝም” ነው ያሉት ዶክተር ዐቢይ።

ሰብሰብ ብለን የኢትዮጵያን ትልቅነት ስናይ የሚጠይቀው ኃላፊነት ከፍተኛ ነውም ብለዋል፡፡

በሻምበል ምህረት

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.