Fana: At a Speed of Life!

አለም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የበለጠ መስራት አለበት-የአለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) አለም አሳሳቢነቱ በየቀኑ እየጨመረ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል መዘጋጀት እንዳለበት የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

በወረርሽኙ በተለያዩ ሀገራት ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች መጠቃታቸውን ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በጄኔቫ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ÷  በኢራን ፣ ጣሊያን እና ደቡብ ኮሪያን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እጅግ አሳሳቢ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ምንም እንኳ ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ቢመጣም ወረርሽኝ በሚባልበት ደረጃ አልደረሰም ተብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአደጋ ጊዜ ፕሮግራም ኃላፊ የሆኑት ማይክ ራያን ሃገራት ለወረርሽኙ የሚያስፈልገውን ሁሉ ዝግጅት ለማድረግ  ጊዜው አሁን ነው ብለዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ የተከሰባቸው ሀገራት ወረሽኙን ለመከላከል የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ኢራን እና ጣሊያንም በሀገራቸው የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ከፍተኛ ጥሪት ላይ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የአለም ግዝፉ የንግድ ማዕከል የሆኑት ዌልስሪት ጆርናል እና  ለንደን በዚህ ቫይረስ መቀዛቀዝ እንደሚታይባቸው ተነግሯል

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.