Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር ሲሞክሩ የነበሩ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ያልሆኑ ግለሰቦችን ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡
 
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና÷ የጸጥታ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ከከተማው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
 
በዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ችግር ለመፍጠር ሲሞክሩ የነበሩ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ያልሆኑ ግለሰቦችን ዩኒቨርሲቲው ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ጠቁመዋል፡፡
 
አሁን ላይም ዩኒቨርሲቲው መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባሩ እንደቀጠለ መሆኑን መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.