Fana: At a Speed of Life!

የዓለማችን ረጅሙ የዕድሜ ባለጸጋ በ112 ዓመታቸው ዓረፉ

አዲስ አበባ፣የካቲት 17፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃፓናዊው የ112 ዓመቱ የአለማችን ትልቁ የእድሜ ባለጸጋ  ቻትሱ ዋታቤ ማረፋቸው ተሰምቷል፡፡

የዓለማችን የረጅም ዕድሜ ባለቤት የሆኑት አዛውንት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት  መለየታቸውን በጃፓን የኒጂጋታ ግዛት አስተዳደር አስታውቋል

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር መጋቢት 5 ቀን 1907 የተወለደውየዕድሜ ባለጸጋው በኒጊታ ውስጥ በሚገኘው አረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ተገልጿል።

የዓለም ድንቃ ድንቅ  መዝገብ ድርጅት ለእድሜ ባለጸጋው በዚህ ዓመት የካቲት 12 በህይወት ያለ በእድሜ ትልቁ ሰው የሚል ስያሜን የሰጣቸው መሆኑ ተነግሯል።

የእድሜ ባለጸጋው በኒጊታ ተወልዶ  ወደ ታይዋን በመሄድ በሸንኮራ አገዳ  እርሻ ላይ  ተሰማርቶ እንደነበርም ነው ተቋሙ የገለጸው፡፡

በኋላ ላይም ወደ ጃፓን ተመልሶ ጡረታ እስኪወጣ ድረስ በኒጊታ ባለው እርሻ ቢሮ ውስጥ ተቀጥሮ ይሠሩ ነበርም ተብሏል ፡፡

የእድሜ ባለጸጋው በፈረንጆቹ ጥር ወር 2019 ከአከባቢው ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ረዥም ዕድሜ የመኖር ምስጢር ከቁጣ በመራቅና ምንጊዜም በፈገግታ መኖር ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

ምንጭ፡-ሲ.ኤን.ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.