Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ነገ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት በ10ኛው የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ህብረት የጋራ ስብሰባ ላይ ለመካፈል ነው።

ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን በስብሰባው ላይ ለመሳተፍም የአውሮፓ ሀብረት ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖለሲ አመራሮችን በውስጡ ያየዘ 20 ልኡካን ቡደን ይዘው ነው የሚመጡት ተብሏል።

የአውሮፓ እና የአፍሪካ ህብረት የጋራ ስብሰባ የፊታችን ሀሙስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድም ይጠበቃል።

የጋራ ስብሰባው በልማት፣ ስራ አጥነት መቀነስ፣ በአረምጓዴ እና ዲጂታል ሽግግር፣ በሰላም፣ በደህንነት፣ በአስተዳደር እና በስደተኝነት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ነው
የሚካሄደው።

ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ከብራሰልስ ከመነሳታቸው በፊት እንደተናገሩት፥ አውሮፓ እና አፍሪካ ተፈጥሯዊ ወዳጆች ናቸው፤ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ
የሚከሰቱ ችግሮችንም እኩል የሚጋፈጡ ናቸው ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ባሳለፍነው ህዳር ወር ላይ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማካሄዳቸው ይታወሳል።

ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም በወቅቱ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ተገናኝተውም ተወያይተው የነበረ ሲሆን፥ ከአፍሪካ ጋር የቀረበ ትብብር መፍጠር የአውሮፓ ህብረት ቀዳሚ ግብ መሆኑን በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።

ፀጥታ እና ስደተኞችን የተመለከቱ ጉዳዮች የሁለቱን አህጉሮች የጋራ ምላሽ እንደሚፈልጉም መግለፃቸውም ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.