Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ጣሊያን አቀኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማምሻውን ወደ ጣሊያን አቅንተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ በጣሊያን ቆይታቸው ከጣሊያኑ አቻቸው ጋር በሚኖራቸው ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ።

በተጨማሪም አቶ ገዱ በጣሊያን ቆይታቸው ከዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት፣ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ ኃላፊዎች ጋር ውይይቶችን እንደሚያደርጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

ከድርጅቶቹ ሃላፊዎች ጋር በሚኖራቸው ውይይት ወቅት ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ የሚያከናውኗቸው የልማት ፕሮጀክቶች በሀገሪቱ ከተጀመረው የሪፎርም ፕሮግራም ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ሃሳብ እንደሚለዋወጡ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.