Fana: At a Speed of Life!

የፊት ጭምብል በመጠቀም የሚከሰት የጤና ችግርን ለመከላከል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፊት ጭምብል (ማስክ) በተለይም በትንፋሽ የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል እንደሚረዳ ይታመናል።

ከዚህ ጠቀሜታው ባሻገር ግን በበዛ መልኩ መጠቀም የራሱ ችግሮች እንዳሉት ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

የፊት ጭምብልን ረዘም ላለ ጊዜ ወይም ሰዓታት ማድረግ ቁስለትን ጨምሮ የቆዳ ላይ ጉዳት እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል ነው የተባለው።

በተጨማሪም በአፍንጫ፣ ጉንጭ እና በጆሮ ዙሪያ ባሉ ህዋሳት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላልም ነው ያሉት ባለሙያዎቹ።

ይህን ለመከላከልም የፊት ጭምብሉን ከሁለት እስከ ሶስት ሰዓታት ውስጥ ቦታ አቀያይሮ መጠቀም እና በየስድስት ሰዓቱ ደግሞ ጭንብሉን መቀየር እንደሚገባ ባለሙያዎቹ ይመክራሉ።

ከዚህ ባለፈም ጭምብሉን ጥቅም ላይ ከማዋልዎ በፊት መመሪያዎቹን ማንበብ እንደሚገባም ነው የሚመክሩት።

እንዲሁም በህክምና ባለሙያዎች የሚመከሩና የጎንዮሽ ጉዳት የሌላቸውን የቆዳ ላይ ቅባቶች መጠቀም ይገባልም ብለዋል።

ጭምብሉን ካወለቁ የተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላም ቆዳን ማጽዳት እና ማለስለሻ መጠቀም አማራጭ ነው።

ምናልባት ጭምብሉን ተጠቅመው ከበድ ያለ የቆዳ ላይ መቆጣት ከተከሰተ ወደ ህክምና መሄድና የህክምና ባለሙያዎችን ማማከር ተገቢ ነው።

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.