Fana: At a Speed of Life!

የአቶ ንዋይ ገብረአብ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለረዥም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት አቶ ንዋይ ገብረአብ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ።

አቶ ንዋይ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ነው።

የቀብር ሰነ ስርዓታቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸው ፣ አድናቂዎቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።

ከ1970ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፕላን ኮሚሽን ውስጥም ለረዥም ዓመታት አገልግለዋል።

አቶ ንዋይ ከኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪነታቸው ባለፈ የኢትዮጵያ የልማት ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.